Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ የ500 ሚሊየን ብር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ፓሮን ትሬዲንግ ከተሰኘው ሀገር በቀል ድርጅት ጋር የ500 ሚሊየን ብር የኢንቨስትመንት ስምምነትተፈራርሟል፡፡
 
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና ፓሮን ትሬዲንግ በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ ምርት ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት።
 
ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና የፓሮን ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ አስሬ ተፈራርመውታል።
 
ድርጅቱ በግብርና ማቀነባበሪያ የተሰማራ ሀገር በቀል ኩባንያ ሲሆን÷ በፓርኩ 500 ሚሊየን ብር ሀብት ፈሰስ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
 
በስምምነቱ መሰረት ድርጅቱ 2 ሄክታር የለማ መሬት የተረከበ ሲሆን÷ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላ ሀገሪቱ በገነባቸው 13 ኢንዱስትሪዎች የውጭ እና ሀገር በቀል ባለሃብቶችን በማስገባት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን እያበረከተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.