Fana: At a Speed of Life!

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የመተላለፊያ መንገዶች እና ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ብዙ ጊዜ ቫይረሱ የሚገኝባቸው እንስሳት በሞቃታማ እና ዝናባማ ደኖች አቅራቢያ ይገኛሉ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የያዘው ሰው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ሕመም ፣ የንፍፊት እብጠት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ድካም ምልክቶችን ያሳያል።

ትኩሳት ከታየ ከ1 እስከ 3 ቀናት ውስጥ (አንዳንድ ጊዜም ረዘም ያለ ጊዜ) ደግሞ በሰውነት ላይ ሽፍታ ይወጣል።

ብዙውን ጊዜ ሽፍታው ፊት ላይ ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚስፋፋ ሲሆን በአጠቃላይ በሽታው ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ይቆያል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ስርጭት የተገደበ ቢሆንም ከሰውነት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት ፣ በቆዳ ላይ ወይም በውስጣዊ ንጣፎች ላይ ለምሳሌ በአፍ ወይም በጉሮሮ፣ በመተንፈሻ አካላት ጠብታዎች እና በተበከሉ ነገሮች ሊተላለፍ እንደሚችል ከጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገፅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.