Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዲጂታል ግብይትን ለማሳደግ የ9 ነጥብ 73 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የአኅጉሩን ዲጂታል ግብይት ለማሳደግ የ9 ነጥብ 73 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የድጋፍ ሥምምነቱን በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽነር አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቡል ካማራ በአዲስ አበባ ተፈራርመውታል፡፡

የገንዘብ ድጋፉን የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በዚህ ዓመት መስከረም ወር ላይ ተወያይቶ ማፅደቁም ተመላክቷል፡፡

በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው የመጀመሪያ ምዕራፍ የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት በአኅጉር ደረጃ የተሰናሰለ አንድ የዲጂታል ግብይት ዕውን ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚፈፀመውን ዲጂታል ግብይት ለማልማት ብሎም የኅብረቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ትግበራ ለማሳለጥ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

ድጋፉ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ዕውን ለማድረግ እና የአፍሪካን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ትግበራ ለማሳለጥ እንደሚያግዝም ተሥፋ ተጥሎበታል፡፡

የተፈቀደው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከፈረንጆቹ 2023 እስከ 2026 ተፈጻሚ እንደሚሆን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.