የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችና ባለሙያዎችን ወደ ትግራይ መላኩን አስታወቀ

By Melaku Gedif

November 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችና የውሃ ባለሙያዎችን በጎንደር ሁመራ መስመር ወደ ትግራይ መላኩን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተጨማሪም የውሃና ተያያዥ አገልግሎቶች ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ከተለያዩ ቁሳቁስ ጋር መላካቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ከዩኒሴፍ በድጋፍ የተገኙ በፀሃይ ሃይል የሚንቀሳቀሱ የውሃ መሳቢያ ፓምፖች በወልዲያ ቆቦ መስመር በኩል ወደ ትግራይ መላካቸው ተገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል ሽረ ከሚገኙ የዩኒሴፍ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹ አስቸኳይ የውሃ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው የማከፋፈልና መሳሪያዎቹን የመግጠም ስራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡