Fana: At a Speed of Life!

ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት ቅንጅታዊ አሰራር  ያስፈልጋል-ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎችን መቋቋም የሚችል  ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት ቅንጅታዊ አሰራር ያስፈልጋል ሲሉ  የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉ የጤና ድንገተኛ አደጋዎችን  ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለውን የዘርፈ ብዙ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ፕሮግራም  ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይፋ  አድርጓል ፡፡

በመድረኩ የተገኙት ሚኒስትሯ  ዶክተር ሊያ ታደሰ  አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰውን የህብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ተጋለጭነትን ከመከላከልና ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አኳያ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የህብረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎችን መቋቋም እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የጤና ስርዓት መገንባት የባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም በትብብር መስራት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡

ዛሬ ይፋ የተደረገው የዘርፈ ብዙ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ፕሮግራም  ዋና ተግባር ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን መቋቋም ላይ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትንም ይበልጥ ያጠናክራሉ ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.