Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለመስጠት ቃል የገባውን 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ገቢ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፓርቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለመስጠት ቃል የገባውን 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ገቢ አደረገ።

የፓርቲው የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገ የብልፅግና ፓርቲ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ በገቡት ቃል መሰረት 100 ሚሊየን ብሩ በጤና ሚኒስቴር የወረርሽኝ መከላከያ አካውንት ውስጥ ገቢ ተደርጓል።

በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን አቶ አወሉ ተናግረዋል።

ፓርቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጋረጠውን ይህን ፈተና ኢትዮጵያ ተጋፍጣ ማለፍ እንድትችል የሚጠበቅበትን ሀላፊነት መወጣቱን እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።

ህብረተሰቡም ከመንግስት እና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ መመሪያዎችን እና የሚቀርቡ ምክሮችን በአግባቡ በመተግበር ራሱን በመጠበቅ የዚህን ቫይረስ ስርጭት በመግታቱ የበኩሉን ሚና እንዲጫወትም አሳስበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.