ስፓርት

በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈች

By Melaku Gedif

November 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው ዓለም ዋንጫ የአራተኛ ቀን ውሎ በምድብ አምስት በተደረገ ጨዋታ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

የማንችስተር ሲቲው የአማካይ ክፍል ተጫዋች ኢልካይ ጉንዶጋን በ33ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር።

ይሁንና ተቀይሮ የገባው የጀርመኑ ፍራይቡርግ ክለብ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሪትሱ ዶአንና የጀርመኑ ቦኸም አጥቂ ታኩማ አሳኖ ባስቆጠሯቸው ግቦች ጃፓን ከመመራት ተነስታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ያልጠተበቀ ውጤት አስመዝግባለች።

በተመሳሳይ ክሮሺያ እና ሞሮኮ ዛሬ 7 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ  0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡