Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር ሀዋሳ ከተማን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር የዘንድሮውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የምታስተናግደውን ሀዋሳ ከተማ ጎብኝተዋል፡፡

በዚህም በከተማው የተሰሩ መሰረተ ልማቶችና እና የከተማ ማስዋብ ስራ ተመልክተዋል፡፡

በአፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ የ17ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዝግጅትን ለመጎብኘት ሐዋሳ ከተማ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ለበዓሉ እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች በመልካም ደረጃ ላይ መሆናቸውን ልዑካን ቡድኑ መመልከቱንም ገልፀዋል።

በዓሉ ከብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መነሻ፣ መድረሻና መመለሻ ድረስ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የፌዴራል የፀጥታ አካላት ከሲዳማ፣ ደቡብ ክልሎች እና ከኦሮሚያ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

የልማት ስራዎችን፣ የህዝቦችን አንድነትና ትስስር ማጠናከር፣ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ማንነት የሚያንፀባርቁ ስራዎችን ማከናወንና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ የዘንድሮው በዓል ዋና ዓላማ መሆኑንም አስረድተዋል።
17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ይከበራል።

በቢቂላ ቱፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.