Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ25 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኙ ወገኖች 25 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚየወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በሃብሩ፣ ጉባላፍቶ እና ቆቦ ከተማ አካባቢ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሰራጨ መሆኑን የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተፈራ ቴሌሮ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ምግብ ድጋፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እያደረሰ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትንና በግብርና ልማት ሥራ መልሶ ማቋቋም የሚስችል ለ2 ዓመት የሚቆይ 68 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ከ68 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በኩል ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን  የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ  ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.