ስፓርት

በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ካሜሮንን 1 ለ 0 አሸነፈች

By Shambel Mihret

November 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌላኛዋ የአፍሪካ ተወካይ ካሜሮን በኳታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በሀገሯ ልጅ በተቆጠረባት ግብ በስዊዘርላንድ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች፡፡

በጨዋታው ብሪል ኤምቦሎ ከሽኮርዳን ሻኪሪ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ቀይሮ ስዊዘርላንድ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን እንድታሸንፍ አድርጓል፡፡

በትውልድ ካሜሮናዊ በዜግነት ስዊዘርላንዳዊ የሆነው ብሪል ኢምቦሎ በዓለም ዋንጫ ካሜሮን ላይ ግብ አስቆጥሮ ደስታውን ባለመግለፅ ለእናት ሀገሩ ያለውን ክብር አሳይቷል፡፡

ኢምቦሎ በካሜሮን የተወለደ ሲሆን÷ ከ6 ዓመቱ ጀምሮ ኑሮውን ስዊዘርላንድ በማድረግ የስዊስ ዜግነትን አግኝቷል፡፡