Fana: At a Speed of Life!

የደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢንጅነሪንግ ከተባለው የቻይና ኩባንያ ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደርባ ሲሚኒቶ ፋብሪካ ሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢንጅነሪንግ ቡድን ከተባለው የቻይና ኩባንያ በደርባን የሲሚንቶ ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በሃገሪቱ ያለውን የሲሚንቶ ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን 80 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ማምረት የሚያስችለውን አቅም ለመፍጠር 282 ሚሊየን ዶላር በሆነ በጀት የማስፋፊያ ስራውን ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል።

ፋብሪካው የሃገሪቱ የሲሚንቶ ፍላጎትን ለመፍታት የራሱን አስተዋጽኦ ሲያበረክት እንደነበርም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

የዛሬው የማስፋፊያ ስምምነት ደግሞ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ከመፍታት አንጻር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡

በስምምነቱ ሥነ-ስርዓት የተገኙት  የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ÷ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራ በዋናነትም የግሉን ዘርፍ በማሳደግ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ የወሰደው የማስፋፊያ እርምጃ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለዚህ ማስፋፊያ ስራ በሚደረገው ስራ የፌደራሉ እና የክልሉ መንግስትም የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የተፈረመው ስምምነት ፋብሪካው በቀን ያመርት የነበረውን ወደ 150 ሺህ ኩንታል ያሳድገዋል ተብሏል፡፡

በይስማው አደራው

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.