የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ከ60 በላይ የመድሃኒት ዓይነቶች የሚያመርተውን ሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

November 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘውን የሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም÷ የሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ የሚያመረታቸው የመድሃኒት ምርቶች ከመጋዘን ጀምሮ እስከ ስርጭት ክፍል ያለውን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡

ዶክተር ሊያ መድሃኒቶቹ ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ለመመረት የሚያልፉበትን መንገድ ማድነቃቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የሳንሼንግ ፋርማቲካል ፋብሪካ ከ60 በላይ የመድሃኒት ዓይነቶች የሚመረቱበት ፋብሪካ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!