ስፓርት

በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች

By Amele Demsew

November 24, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ጨዋታ የአምስተኛ ቀን ውሎ በምድብ ስምንት በተደረገ ጨዋታ ፖርቹጋል ጋናን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ የፖርቹጋልን የመጀመሪያ ግብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በፍጹም ቅጣት ምት በ65 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ጃኦ ፍሊክስ እና ራፋይል ሌዮ ደግሞ 78 ኛው እና 80ኛው ደቂቃ ላይ የፖርቹጋልን ሁለተኛ እና ሶስተኛ ግቦች ማስቆጠር ችለዋል፡፡ ጋናን ከሽንፈት ያላዳነቻቸውን ሁለት ግቦች አንድሬ አየው እና ኦስማን ቡካሪ በ73ኛው እና 89ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡ በዚህም እስካሁን አፍሪካን ወክለው በዓለም ዋንጫ ከተሳተፉት ሀገራት መካከል ጋና በመጀመሪው ዙር ግብ ያስቆጠረች ብቸኛ ሀገር ሆናለች፡፡