ስፓርት

በዓለም ዋንጫው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ

By Feven Bishaw

November 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል የምትሳተፍበትን ጨምሮ አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

በዚህም በምድብ ሁለት የተደለደሉት ዌልስ ከኢራን ቀትር 7 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን ÷ በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት እንግሊዝ ከአሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ አንድ የሚገኙት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ኳታር ከአፍሪካዊቷ ሴኔጋል ቀን 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት ኔዘርላንድስ ከኢኳዶር ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያካናውኑ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡