ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ጎል ያስቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡
በዓለም ዋንጫው በምድብ 8 ትናንት ምሽት ፖርቹጋል ጋናን ስታሸንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፍጹም ቅጣት ምት የውድድሩን የመጀመሪያ ጎሉን በዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ደግሞ በተሰለፈባቸው 192 ጨዋታዎች 118ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።
ይህን ተከትሎም በተከታታይ አምስት የዓለም ዋንጫዎች ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል።
ሮናልዶ በ2006ቱ የጀርመን የዓለም ዋንጫ፣ በደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ፣ በብራዚል የዓለም ዋንጫ፣ በ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ እና በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ በተከታታይ ጎል ማሰቆጠር ችሏል፡፡
ሮናልዶ 192 ጨዋታዎችን ለሃገሩ ያደረገ ሲሆን 118 ጎሎችን በማስቆጠር የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡