Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የነጭ ሪባን ቀን ላይ ለመታደም ሐዋሳ ከተማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዓለም ለ31ኛ እና በኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የነጭ ሪባን ቀን ላይ ለመታደም ሐዋሳ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቷ ሐዋሳ ከተማ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ እና ሌሎች የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዓለም አቀፉ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን (የነጭ ሪባን ቀን) በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ እንደሚገኝ ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.