Fana: At a Speed of Life!

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በመሬት ዝርፊያ ከተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች ውስጥ 12ቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመሬት ላይ ሲደረግ በቆየ የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ37 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከመሬት ዝርፊያ ጋር በተያያዘ ሲያደርግ በቆየው የማጣራት ስራ በክፍለ ከተማው የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች፣ባለሙያዎች፣ ደላሎችና በዚህ ድርጊት የተሳተፉትን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ   እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ቀሪዎችን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን÷ተጨማሪ የማጥራት ስራም እየተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል:-

  1. ለምለም አባይነህ፡- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 4 ዋና ስራ አስፈፃሚ
  2. አቶ ከፍያለው አሰፋ፡- የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ
  3. አቶ ዋሲሁን ሰውነት፡- የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ
  4. አቶ ኢብራሂም ሀሰን፡- የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ ሲሰጡ የነበሩ)
  5. አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ
  6. አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ
  7. አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉግለሰቦች
  8. አቶ አየለ ጉቱ
  9. አቶ ጎሳዬ ደሜ
  10. አቶ በፍቃዱ ወንደሰን
  11. አቶ ሮባ ደበሌ
  12. አቶ መታሰቢያ አባተ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.