Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ ነው – ሰመሪታ ሰዋሰው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ገለጹ፡፡

በመንግስትና በዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ትብብር በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በመልሶ ማቋቋም ጉዳዮች ላይ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ  ውይይት ተካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው÷ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በመልሶ ማቋቋምና በሌሎችም የልማት ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ሃላፊዎችና ተወካዮች የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት አጋር እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ማስገንዘባቸውንም የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.