Fana: At a Speed of Life!

“ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል”- የአክሱም፣ ዓድዋና ሽረ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የትግራይ ህዝብ የሰላም አየር መተንፈስ ጀምሯል፤ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል” ሲሉ የአክሱም፣ ዓድዋና ሽረ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች በሰላም ስምምነቱ እጅግ መደሰታቸው ገልጸው÷ ለተግባራዊነቱ ሁሉም በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢዜአ ያነጋገራቸው የሽረ፣ አክሱምና ዓድዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት፤ የሰላም ስምምነቱ መላ ኢትዮጵያውያንን ባለ ድል ያደረገ ነው፡፡

በጦርነቱ ህይወት ተገብሯል፣ ሃብትና ንብረት ወድሟል፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ችግር ሊደርስባት አይገባም ብለዋል።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማቾች ነን፤ ችግሮቻችንን በሰላም በመፍታት አንድ መሆናችንን የምናሳይበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ በሰላም ስምምነቱ መላ ኢትዮጵያውያን አትራፊዎች ነን ብለዋል።

በመሆኑም ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ወደ መደበኛ ኑሯችን እንድንመለስ ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል በማለትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.