የሀገር ውስጥ ዜና

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 234 ተማሪዎች አስመረቀ

By Alemayehu Geremew

November 26, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 234 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተማሪዎቹ በሕክምና እና ጤና በቅድመ እና ድህረ ምረቃ ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 123ቱ ወንዶች ሲሆኑ 111ዱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።