Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ውሎ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ሲቀጥል አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታወች ይከናወናሉ፡፡

በዚሁ መሰረት በምድብ አምስት የተደለደሉት ጃፓን እና ኮስታሪካ ቀን 7 ሰዓት ላይ እንዲሁም በእዚሁ ምድብ የሚገኙት ስፔን ከጀርመን ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

በዛሬ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ ሥድስት የሚገኙት ቤልጂየም ከሞሮኮ ቀን 10 ሰዓት ላይ እንዲሁም ክሮሽያ ከካናዳ ምሽት 1ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያካሂዱ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡

ቀደም ብሎ በተካሔደው የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ሞሮኮ ከክሮሺያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ሲለያዩ÷ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ1፣ ስፔን ኮስታሪካን 7 ለ 0 እንዲሁም ቤልጂየም ካናዳን 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ትናንት በተካሔዱ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች÷ አውስትራሊያ ቱኒዚያን 1 ለ 0፣ ፖላንድ ሳዑዲ ዓረቢያን 2 ለ 0፣ ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 እንዲሁም አርጀንቲና ሜክሲኮን 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.