Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ ዞን ቻግኒ ከተማ የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዶክተር ይልቃል ከፋለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት÷ ክልላችን ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት የሚገኝበት በመሆኑ ሃብቱን በሚፈለገው ደረጃ በማልማት ከዘርፉ የምናገኘውን ተዋጽኦ ማሳደግ አለብን።

ዕድገትና ብልጽግናችን የሚረጋገጠው በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ስንችል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል÷ በሰብል ልማት ያስመዘገብነውን ስኬት በሌማት ትሩፋት መርሐግብር አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የተቀናጀ ሥራ መሥራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዓላማ÷ ተመጣጣኝ ምግብ በብዛትና በጥራት በገበያው እንዲኖር ማስቻል እና ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ የሆነ የምግብ ሥርዓት መገንባት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመርሐ ግብሩ ዋና ግብ÷ ስጋ፣ እንቁላል፣ ማርና ወተት የቅንጦት ምግቦች ሳይሆኑ በቀላሉ የሚገኙ አማራጮች እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.