Fana: At a Speed of Life!

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ወደ ትግራይ ክልል 32 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ድጋፍ ተደራሽ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት እና ህወሓት ያደረጉትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትግራይ ክልል 32 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህልና ከ360 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተደራሽ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሺፈራው ተክለማርያም መንግስት የሰላም ስምምነቱን መሰረት በማድረግ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል ያለገደብ ተደራሽ እያደረገ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአራት ኮሪደሮች በየብስ እንዲሁም በመቀሌና በሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል እርዳታ ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ እስከ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መንግስት በራሱ አቅም 13 ሺህ ሜትሪክ ቶን ጥራጥሬና አልሚ ምግብ÷ በእርዳታ ድርጅቶች በኩል ደግሞ 19 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ተናግረዋል፡፡

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ወደ ትግራይ 32 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ተደራሽ ተደርጓል- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት እና ህወሓት ያደረጉትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ትግራይ ክልል 32 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህልና ከ360 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተደራሽ መደረጉን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሺፈራው ተክለማርያም እንደገለጹት÷ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ እስከ ሕዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መንግስት በራሱ አቅም 13 ሺህ ሜትሪክ ቶን ጥራጥሬና አልሚ ምግብ እንዲሁም በእርዳታ ድርጅቶች በኩል 19 ሺህ ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ወደ ትግራይ ክልል ልኳል፡፡

ባለፉት ሳምንታት ወደ ክልሉ የተላከው የሰብዓዊ እርዳታም ከ2 ሚሊየን በላይ የክልሉ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከምግብ አቅርቦት ባለፈ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ ማጓጓዣ የሚውል ከ360 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ወደ አካባቢው መላኩን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ከፍተኛ መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ፣ ለትምህርት ቤቶችና ለአካባቢው ነዋሪ የውሃና ለንጽህና መጠበቂያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአማራና አፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች በነበረው ግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ መንግስት እያደረገ ካለው ጥረት ባለፈ የማህበረሰቡን ተሳትፎ አድንቀው÷ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት አስተባባሪ ኮሚቴ አደራጅቶ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበው÷ መደበኛ አገልግሎቶችን ከማስጀመር ጎን ለጎን ዜጎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እስከሚመለሱ ሰብዓዊ ድጋፉን አጠናከሮ ለመቀጠል በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

መንግስት ሀብት ከማሰባሰብ ባለፈ የእርዳታ ድርጅቶችን አቅም ለመጠቀም እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው÷ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መንግስት በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.