የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የ90 ቀናት እቅድ ተግባራት አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ጎበኙ

By Feven Bishaw

November 27, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የ90 ቀናት እቅድ ተግባራት አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በጉብኝታቸው÷ በክፍለ ከተማው በ90ቀናት እቅድ ተካተው ወደ ተግባር ተገብቶ እየተከናወኑ የሚገኙ የአገልግሎት ማሻሻያና የመልካም አስተዳደር ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል፡፡

እንዲሁም የከተማ ግብርና፣የዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ታሣቢ ያደረጉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት በክፍለ ከተማው እየተሠሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም በዘጠና ቀናት እየተሠሩ ያሉ ስራዎች በእቅዳቸው መሠረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ መገንዘብ መቻሉን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡