Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ምክትል ዋና ፀሃፊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሊ ጁንሁዋ ኢትዮጵያ በምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ዋና ጸሐፊው አዲስ አበባ ሲገቡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የፓፓዋ ኒው ጊኒ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ቲሞቲ ማሲዩ በዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ሲገቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላመርዳሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን÷በጉባኤው ለመታደም እንግዶች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.