ስፓርት

ስፔንና ጀርመን አቻ ተለያዩ

By Mekoya Hailemariam

November 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) – የምድባቸውን ሁለተኛ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ያደረጉት ስፔንና ጀርመን ሳይሸናነፉ ቀርተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች 90 ደቂቃውን 1ለ1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ጀርመን በአንድ ነጠብ በምድቧ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ስፔን በአንፃሩ በ4 ነጥብ ምድቡን አየመራች ትገኛለች።

በዚህ ምድብ ሚገኙት ጃፓንና ኮስታሪካ እኩል ሶስት ነጥብ አላቸው።

ጀርመን የምድቧን የመጀመሪያ ጨዋት በሽንፈት የጀመረች ሲሆን ስፔን በአንፃሩ በሰፊ ጎል ልዩነት ማሸነፏ የሚታወስ ነው።