በዛሬው የዓለም ዋንጫ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛ ቀኑን በያዘው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውሎ ካሜሮን እና ጋና የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡
በዚሁ መሰረት በምድብ ሰባት የተደለደሉት አፍሪካዊቷ ካሜሮን እና ሰርቢያ ቀን ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡
በዚሁ ምድብ የተደለደሉት ብራዚል እና ስዊዘርላንድ ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ ስምንት የተደለደሉት ጋና እና ደቡብ ኮሪያ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ፖርቹጋል እና ኡራጋይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡
ትናንት በተካሔዱ የዓለም ዋንጫ አራት ጨዋታዎች ኮስታሪካ ጃፓንን 1 ለ 0 አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ቤልጂየምን 2 ለ 0፣ ክሮሺያ ካናዳን 4 ለ 1 ሲያሸንፉ÷ ስፔንና ጀርመን 1 አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡