Fana: At a Speed of Life!

በካሊፎርኒያ የተከሰተው ድርቅ የአሜሪካን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ይጥላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያስተናገደችው ከባድ የድርቅ አደጋ ከሠብል ምርት ታገኝ የነበረውን ቢያንስ 3 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ገቢ እንዳሳጣት ጥናት አመላከተ፡፡

ካሊፎርኒያ ከአሜሪካ ግዛቶች በግብርና ምርቷ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ናት፡፡

በካሊፎርኒያ የምግብ እና ግብርና ክፍል የተዘጋጀው ጥናት እንዳመለከተው በፈረንጆቹ 2021 እና 2022 ብቻ በመካከለኛው ሸለቆ የሚገኘው የገጸ ምድር ውሃ በ43 በመቶ ቀንሷል፡፡

ይህም የግዛቷ ገበሬዎች ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬታቸውን ሳያለሙ ጦም እንዲያሳድሩ አስገድዷቸዋልም ነው የተባለው፡፡

መካከለኛው ሸለቆ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ውሃ እንደልብ ይገኝ በነበረበት ወቅት በአሜሪካ ለምግብነት እንዲውል ከሚሰበሰበው የግብርና ምርት ውጤቶች 25 በመቶውን ይሸፍን እንደነበርም አር ቲ አመላክቷል፡፡

ከግብርና ምርቶቹ መካከል 40 በመቶውን የሚሸፍነው የፍራፍሬ እና የለውዝ ምርት ሲሆን ወይን እና አትክልቶችም በስፋት ይመረቱ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.