የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙ ተገለጸ

By Tibebu Kebede

March 28, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው በፌስቡክ ገጸቸው ባወጡት መረጃ፥ በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማቆያ ያሉ አጠቃላይ ሰዎች13 መሆናቸውን ገልጸዋል።