የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው

By Tamrat Bishaw

November 29, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 67ኛው የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት ጉባዔ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ እየተካሔደ ነው።

“የጥራት ሚና ለኢንዱስትሪ ዕድገት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሔደ በሚገኘው ጉባዔ ላይ ከ20 በላይ ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ባለድርሻ አካለት አየተሳተፉ ነው።

ጉባዔው በአራት ቀናት ቆይታው ምርቶችን ወደ ዓለም ገበያ ለማምጣት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

ጉባዔው በኢትዮጵያ መካሔዱ ለሀገሪቱ ገፅታ ግንባታ ከሚኖረው ሚና ባሻገር አህጉራዊ ግንኙትን እንደሚያጠናክር ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት በፈረንጆቹ በ1977 ነው የተቋቋመው፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ