የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በስልክ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 28, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በትናንትናው ዕለት በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስፈልጉ ወሳኝ ድጋፎች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።