የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 28, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።