Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከ617 ሺህ በላይ ሰዎች ከኤች አይ ቪ ጋር ይኖራሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013/14 በተሠራ ግምታዊ ቀመር መሠረት በኢትዮጵያ ከ617 ሺህ በላይ ሰዎች ኤች አይ ቪ በደማቸው ይኖራል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የዓለም የኤድስ ቀን አከባበርን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ስጥተዋል።

በመግለጫቸውም፥ የዘንድሮ የዓለም የኤድስ ቀን “ፍትሐዊና ተደራሽ የኤችአይቪ/ኤድስ አገልግሎት ” በሚል መሪ ሐሳብ በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ ነገ ይከበራል ብለዋል፡፡

ኤች አይ ቪ መከሰቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ በዓለም ከ40 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና 38 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህል ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ይገኛል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በ2013/14 የተሠራው ግምታዊ ቀመር እንዳመላከተውም ከ617 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይኖራል፡፡

በሀገራችን የኤችአይቪ የስርጭት መጠን መቀነሰ ቢቻልም አሁንም በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት እና ቸልተኝነት አለ ብለዋል ዶክተር ሊያ በመግለጫቸው፡፡

በመራኦል ከድር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.