የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች የፊታችን ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የቨርቺዋል ኮንፈረንስ ሊያካሂዱ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት(ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች የፊታችን ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያተኮረ የቨርቺዋል ኮንፈረንስ ሊያካሂዱ ነው።
ኮንፈረንሱ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭትን በቀጣናው በቅንጅት መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር መሆኑን የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናግረዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆናቸው ተመላክቷል።
በስላባት ማናዬ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision