የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ ኤጀንሲዎች 54 ሺህ 400 ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ

By ዮሐንስ ደርበው

November 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመድ ኤጀንሲዎች በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተፈናቀሉ እና በአደጋ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚውል የ18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡

በሁለቱም ክልሎችለአራት ዓመታት የሚቆየው መርሐ ግብር 54 ሺህ 400 የሚጠጉ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረጉት የስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ (ኤስ.ዲ.ሲ) እና በስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ሲዳ) ናቸው፡፡

ዓለምአቀፉ የምግብ እና ግብርና ድርጅት (ፋኦ)፣ በተመድ የሰብዓዊ ሰፈራ ፕሮግራም (ዩኤን-ሃቢታት) እና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ.ኦ. ኤም) ከኤጀንሲዎቹ ጋር በመቀናጀት ፕሮጀክቱን እንደሚደግፉ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፕሮጀክቱ ማህበረሰብ አቀፍ ትስስርን ለማጠናከርና ለማቋቋም፣ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችበፈቃደኝነት ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ፣ ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረው እንዲሰፍሩ እና ድጋፍ ለማድረግ ይሠራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!