Fana: At a Speed of Life!

ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የዱቄት ወተት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት ነው – የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገባና ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም (NIDO FORTIFIED 400g Full Cream Milk Powder, Batch No. 0000039688) የተባለ የዱቄት ወተት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ።

እንደ ባለስልጣኑ ገለፃ፥ የምርት መያዣ ዕቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ድብቅ ጽሁፍ (Barcode) ሲነበብ የምርቱ የመጠቀሚያ ጊዜ እ.ኤ.አ 09/2021 የሚል ሲሆን፤ ከምርት መያዣ እቃው (ጣሳው) ላይ የተፃፈው ደግሞ እ.ኤ.አ 01/2024 ይላል።

በመሆኑም በድብቅ ጽሁፉ (Barcode) የሚወጣው የምርቱ ሙሉ መረጃ ላይ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ፥ ኒዶ ፎርቲፋይድ 400 ግራም ፉል ክሬም የዱቄት ወተትን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ባለስልጣኑ አሳስቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.