ዓለምአቀፋዊ ዜና

የ“አይ ኤስ” መሪ አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ ተገደለ

By Alemayehu Geremew

December 01, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ “ካሊፍ” ብሎ የሚጠራው የ “አይ ኤስ አይ ኤስ” መሪ አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ መገደሉ ተነግሯል፡፡

አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ በውጊያ ላይ መገደሉን የአይ ኤስ ሽብር ቡድን ምክትል መሪ ማስታወቁን አርቲ እና ሬውተርስን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ መሪው የተገደለበትን ሁኔታ ፣ ጊዜ እና ቦታ አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ አለመስጠቱ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

“አይ ኤስ አይ ኤስ” ፣ ቀደም ሲል “አይ ኤስ አይ ኤል” በኢራቅ ደግሞ አልቃይዳ በመባል የሚጠራው የሽብር ቡድን በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2004 በአቡ ሙስዓብ አል ዛርቃዊ መመስረቱ ይነገራል፡፡