ቴክ

በይነመረብን ከምድራችን ውጭም በመዘርጋት መጠቀም ይኖርብናል- የኢንተርኔት አባት

By ዮሐንስ ደርበው

December 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበይነመረብ ግንኙነትን ከምድራችን ውጭ ባሉ ቦታዎች በመዘርጋት መጠቀም ይኖርብናል ሲሉ የኢንተርኔት አባት በመባል የሚታወቁት ቪንቶን ሰርፍ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቪንቶን ሰርፍ ስለ በይነ መረብ አስተዳደር እና የወደፊት እጣ ፋንታ ምልከታቸውን አጋርተዋል።

በበይነ መረብ ግንኙነት ውስጥ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አዲስ ዓለም ውስጥ እየገባን በመሆኑ የበይነመረብ ግንኙነቶች ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ መስፈርቶች ማሰብ ይገባል ብለዋል፡፡

በይነመረብን ለበለጠ ልማት ስራ ላያ ለማዋል አሁን ከምንኖርበት ምድር ውጭ ባሉ ሌሎች ፕላኔቶች መዘርጋት ይኖርብናል ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!