የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒዶ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ለመሥራት ያለውን ፍላጎት ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

December 01, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) በተመረጡ ዘርፎች ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በጋራ ለመሥራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም የኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መምከራቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ጃንጥራ እንደገለጹት÷ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የሚያግዝ ዓላማ ይዞ ለሚመጣ ማንኛውም ዓለም አቀፍ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል፡፡

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ ሀገር ሲገቡ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ዕቅድ መያዝ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የዩኒዶ ተወካዮች በበኩላቸው÷ በዋናነት በአቅም ግንባት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ማህበራዊ ግዴታዎችን መወጣት ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!