የሀገር ውስጥ ዜና

ለአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

By Melaku Gedif

December 01, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ህጻናት መርጃ ድርጅት (የኒሴፍ) መቀሌ ለሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኒሴፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ እንደገለጸው÷በትግራይ ክልል የሕክምና መሳሪያዎችን በተለያዩ አካባቢዎች የማሰራጨቱ ሒደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት ለአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ለድንገተኛ ህክምና የሚያገለግሉ የመመርመሪያ ኪቶች እና የተለያዩ መድሃኒቶች ድጋፍ ማድረጉን ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የማዋለጃ መሳሪያዎች፣ አስቸኳይ እርዳታ ለሚስፈልጋቸው ህጻናትና እናቶች የሚውል አልሚ ምግብ እና ወተት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶችን ማስረከቡን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!