Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ህብረት መሪነት የተጀመረው የሰላም ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የተጀመረው የሰላም ማምጣት ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መሪዎቹ መግለጫውን የሰጡት የተባበሩት መንግስታ ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብትን በተመለከተ በጋራ በሚያካሂዱት ስብሰባ መክፈቻ ላይ ነው፡፡

ስብሰባው በዋናነት በአፍሪካ ሀገራት ላይ ባለው የሰብዓዊ መብት እና የአየር ንበረት ለውጥ ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተገልጿል፡፡

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በመግለጫቸው ÷በኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የተጀመረው የሰላም ማምጣት ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመንግስት እና በህወሓት መካከል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ነው ያሉት።

የተደረገው ስምምነት ተፈጻሚነትን በተመለከተም በሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች የተጀመረው ንግግር ተስፋ ሰጭ መሆኑን ዋና ጸሃፊው አውስተዋል።

ህገመንግስታዊ ባልሆነ መልኩ የሚደረጉ የመንግስት መቀየር ሙከራዎች ተቀባይነት እንደሌላቸውም አንቶኒዮ ጉተሬዝ አጽንኦጽት ሰጥተዋል።

የአፍሪካ አህጉር ያላትን የመልማት አቅም በመጠቀም ልትለማ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ሙሳ ፋኪ ማሃመት በበኩላቸው ÷የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ለተጀመረው የሰላም ስምምነት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በለይኩን አለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.