ስፓርት

የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

By Tamrat Bishaw

December 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

ቤልጂየም በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፉን ሳትቀላቀል መቅረቷን ተከትሎ ነው አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት፡፡

በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ቤልጂየም ካናዳን 1 ለ 0 ብታሸንፍም÷ በሞሮኮ 2 ለ 0 በመሸነፏ እና ወደ ጥሎ ማለፍ በተደረገው ፍልሚያ ከክሮሺያ ጋር ያለምንም ግብ አቻ በመለያየቷ ስኬት እርቋት ተሰናብታለች፡፡

የ49 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በፈረንጆቹ 2016 የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!