የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል የሙስና ወንጀልን መከላከል የሚያስችል ኮሚቴ ተቋቋመ

By ዮሐንስ ደርበው

December 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሙስና ወንጀልን ለመከላከል እና የወንጀሉን ተዋንያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ሰባት አባላት ያሉት ክልላዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ኮሚቴው በተለያዩ መዋቅሮች በተደራጀ መልኩ የሚፈፀም ሙስናን በመከላከል ወንጀለኞች ለሕግ ቀርበው ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የፀረ ሙስና ክልላዊ ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣና ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያመጣ ህብረተሰቡ ሙሉ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ህብረተሰቡ የሙስና ተዋንያንን በተመለከተ ያለውን መረጃ በቀጣይ ቀናት ኮሚቴው ይፋ በሚያደርጋቸው አድራሻዎች በመላክ ሙስናን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆንም ተጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!