የሀገር ውስጥ ዜና

ዲፕሎማቶች በአማራ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ

By Feven Bishaw

December 02, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ ዲፕሎማቶች በአማራ ክልል የአምራች ኢንደስትሪዎችን ጎበኙ።

ለቀናት የተለያዩ ስልጠናዎች የወሰዱት ዲፕሎማቶቹ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡልልታ በተገኙበት በደብረብረሃን ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እና የተለያዩ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።

የጉብኝት መርሐ ግብሩ ዲፕሎማቶቹ ኢትዮጵያን በሚወክሉባቸው ሀገራት የውጭ ምንዛሬን እና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምን መስራት እንዳለባቸው ግንዛቤ መፍጠርን ያለመ ነው ተብሏል።

ዲፕሎማቶች ሀገሪቷ ያላትን የመልማት አቅምና የአምራች ኢንዱስትሪው ያለበትን ደረጃ ማየት የሚያስችላቸውን ጉብኝት ትናንት በኦሮሚያ ክልል ጉብኝት ማካሄዳቸው ተመላክቷል፡፡

በሀብታሙ ተክለስላሴ