የከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ካሰባሰበው ድጋፍ ለአካል ጉዳተኞች አበረከተ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ ካሰባሰበው ድጋፍ ለአካል ጉዳተኞች አበረከተ።
ድጋፉ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ህብረት ፌደሬሽን የተበረከተ ሲሆን በማህበሩ በኩል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ያበረከተው ድጋፍ የንፅህና መጠበቅያ ቁሳቁሶችና ምግብን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞች ማህበሩ የሚገኝበት ቅጥር ጊቢ ለአካል ጉዳተኞች የማይመች በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ወጪ በአዲስ መልክ እንዲገነባ ውሳኔ መተላለፉን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።