የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉይሳ ፍራጎሳ ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

December 02, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉይሳ ፍራጎሳ ጋርተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በባህል፣ በስፖርት፣ በታሪክ እና የሁሉቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ቀጄላ የኢትዮጵያ እና የፖርቹጋል ግንኙነት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ግንኙነቱን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡