Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፈረንሳይ ፈጣን ባቡሮች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ለማመላለስ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለውን የአልጋ መጨናነቅ ለመቀነስ ፈጣን ባቡሮች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለማመላለስ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።

ፈረንሳይ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ፈጣን ባቡሮችን ነው ለዚህ አገልግሎት እየተጠቀመች የሚገኘው።

ወደ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታልነት የተቀየሩት እነዚህ ፈጣን ባቡሮች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ከአንደኛው የሀገሪቱ ክፍል ወደ ሌለኛው በማመላለስ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ሳሙ የተሰኘው የድንገተኛ አደጋዎች አገለግሎት ድርጅት ፕሬዚዳንት ፍራንኮስ ብራውን ከአምቡላንስና ሄሊኮፕተር የበለጠ በርካታ ቦታ በፈጣን ባቡሮቹ ላይ አለ ብለዋል።

የህሙማን አልጋዎች በባቡሩቹ ወንበር ላይ እንዲያያዙ የተደረገ ሲሆን በባቡሩ ውስጥ የሚገኘው ካፌም ወደ ህክምና ቦታ መቀየሩ ተነግሯል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Exit mobile version