Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በ82 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በ82 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የትምህርትና የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች አቶ ኦርዲን በድሪና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመረቁ፡፡

በሥነ -ስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት÷ በክልሉ በገጠር ወረዳዎች የትምህርትና የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በክልሉ በከተማና በገጠር ወረዳዎች ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የተማሪዎችን የትምህርት መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስ እና የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ ልማት ግንባታዎች ጉልህ ሚና ይኖራቸዋልም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይ ብቁና ጥራት ያለው መምህርና የትምህርት አመራር በመመደብ የትምህርት ሴክተሩን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ አርሶ አደሩ የሚያመርታቸውን ምርቶች ወደ ገበያ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል።

የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን የመጠበቅና የመንከባከብ ሀላፊነት የሁሉም ዜጋ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.