የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ከአምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

December 02, 2022

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ በእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ መክረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ የአሜሪካ መንግስት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት  አድንቀው÷ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአጎዋ በመታገዷ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ጫና ለማስቀረት አሜሪካ ጉዳዩን እየተከታተለችው ነው ማለታቸውን የደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡