Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ እየተካሄዱ ባሉ ኢኮኖሚያዊ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ7ኛው የአፍሪካ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ እና በአፍሪካ ኅብረት 5ኛ ልዩ የኢኮኖሚ ሲምፖዚየም ላይ በናይጄሪያ አቡጃ አየተሳተፈች ነው፡፡

በሲምፖዚየሙ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ፣ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት እና የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማጎልበት ረገድ ኢኮኖሚያዊ ቀጠናዎቹ የሚወጡት ሚና ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ÷ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪው ልማት ዘርፍ ያስመዘገበችውን ውጤት ፣ ቀጠናዊ አስተዋፅዖ እና የፖሊሲ ለውጥ አስረድተዋል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ በሥራ ዕድል ፈጠራ ፣በወጪ ንግድ ዕድገት እንዲሁም በክኅሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያላትን ልምድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር አካፍለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.